የሃላፊዉ መልክት

 

/photo

                                                                                                            አቶ ካንቹላ ካንቤ 

                                              የኤጀንሲው ዳይሬክተር

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ የሲዳማ ክልል መመስረት ጋር ተያይዞ በአዋጅ ቁጥር 003/2012 ዓ.ም መሰረት የተቋቋመ መንግስታዊ ተቋም ስሆን የሙያ ብቃት ምዘና ወስደው ተወዳዳርና ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን በክልልም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚኖሩ ኢንዳስትርዎች ተወዳድረው ወደ ሥራ ገበያ በመቀላቀል ለሀገርቱ ብልጽግና ጉዞ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ዘጎችን ማፍራት ዋና ዓላማ አድርጎ የሚሰራ ተቋም ነው፡፡ በዚህ መነሻ በኤጀንሲው አገልግሎት የሚያገኙ አካላት፡- የግል ስልጠና ተቋማት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የመንግስት ተክኒክና ሙያ ተቋማት፣ ኢንዳስትርዎች፣ተመዛኝ ባለሙያዎች፣ የትኩረት ዘርፍ መሪ መ/ቤቶች፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አንቀሳቃሾች…ወዘተ ስሆኑ ከነዚህ ተቋማት ለምዘና የሚቀርቡ ባለሙያዎች ብቃት በምዘና በማረጋገጥ ብቁ የሆኑትን ወደ ሥራ ገበያ እንድቀላቀሉ የማድረግ ሥራ በትኩረት ይሠራል፡፡ የኤጀንሲው ቋም መርህና መሰሶ ጥራት ያለውን የምዘና አገልግሎት በማካሄድ በሙያው የተመሰገነ ባለሙያ እንድፈጠርና ለዝህም የሚያግዙ ብቁ መዛኞችንና ደረጃውን የጠበቀ የምዘና መሳርያዎችን ማዘጋጀት፣ ግልጽና ተጠያቂነት ያለውን አሠራር መዘርጋት፣ ብልሹ አሠራርን ታግሎ በማስተካከል ለኤጀንሲው የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት በትጋት እየተሰራ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የምዘና አገልግሎት አሰጣጡን የበለጠ ፍሬያማና ቀልጣፋ እንድሁም ጥራቱን የጠበቀ ለማድረግ ሁሉንም ሥራዎች በቴክኖሎጂ አስደግፎ መስራትና አሰራሮችን ማዘመን አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ይህ ዌብ ሳይትና የሰርተፍኬት ትክክለኛነት የሚያረጋግጥ ሶፍትዌር በልጽጎ ሥራ ላይ እንድውል ተደርጓል፡፡