Skip to main content

የእቅ/በጀት/ዝግ/ ክት/ ግምገማ  ዳይሬክቶሬት

  • የሥራ ቡድኖችን ሥራ ያቅዳል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ውሳኔ በሚያሥፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣
  • ባለሙያዎችን የአቅም ክፍተት በማጥናት አቅማቸው የሚገነባበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
  • ለሥራ ቡድኖችና ባለሙያዎች የሚያስፈልጉ ግብአቶች እንዲሟሉ ያደርጋል፣
  • የመሥሪያቤቱን ስትራቴጂክና አመታዊ እቅድና በጀት ዝግጅት፣ የክትትልና ድጋፍ፣ የግምገማና ግብረ መልስ ሥራዎችን በኃላፊነት ይመራል፣ ያስተባብራል፣
  • እቅድና በጀት ዝግጅትና ሪፖርት፣ የግምገማና ግብረመልስ ሥራዎች ውጤታማና ቀልጣፋ እንዲሆኑ ያሠራር ስርዓቶችን ይዘረጋል፣
  • የጸደቀው እቅድና በጀት ለሥራ ክፍሎች በአግባቡ እንዲደለደል በማድረግ ያሳውቃል አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ግብረ-መልስ ይሠጣል፣
  • የሥራ ክፍሎች እቅድና በጀት ዝግጅት ሥራን እና አፈፃፀምን ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይገመግማል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፡፡
  • የበጀት ዝውውር ጥያቄ ሲቀርብ አግባብነቱን በመመርመር የውሳኔ ሃሳብ ለበላይ ኃላፊው ያቀርባል ሲወሰንም ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
  • እቅድና በጀት አፈጻጸምና አጠቃቀም ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮች አማራጭ የመፍትሄ ሀሳብ በማመንጨት ለዉሳኔ ያቀርባል፣ ሲወሰን ተግባራዊ ያደርጋል፣