Skip to main content

የኤጀንሲው ስልጣን፣ ተግባርና ሀላፊነት

  • በፌደራልም ደረጃ የተዘጋጁ የቴ///ሥልጠና ስትራቴጂዎችን መነሻ በማድረግ በኤጀንሲው የሚሰሩትን ሥራዎች ለይቶያቅዳል፣ ዕቅዱንም በተቀመጠው መርሃ ግብር መሰረት ተፈፃሚ ያደርጋል፡፡
  • በኤጀንሲው የታቀዱ ተግባራትን ለማስፈፀም የሚያስችል የበጀት ዕቅድ በማዘጋጀት ለክልሉ መንግስት ፕላንና ፋይናንስ ቢሮ ያቀርባል፤ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል፡፡
  • የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና እና  የሰርተፊኬሸን ተግባራትን በሚመለከት ስትራቴጂክ ዕቅድ ያወጣል፤ ተግባራዊም ያደርጋል፣፤ በፌደራል ደረጃ በተቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት እየተፈፀሙ መሆኑን ይከታተላል፡፡
  • የኤጀንሲው የሙያ ብቃት ደረጃና ጥራት ለማሳደግ በሰው ኃይልና ቁሳቁሰ አቅርቦት የተሟላ በማድረግ ምቹ የሥራ ሁኔታይፈጥራል፡፡
  • በሴክተር መስሪያ ቤቶች እና በኢንዱስትሪዎች ትብብር የተዘጋጁ ረቂቅ የሙያ ብቃት ምዘና መሳሪያዎች ይገመግማል፤ ያስተካክላል፡ያጸድቃል፣የፀደቁት የሙያ ብቃት ምዘና መሳሪያዎችን ጥቅም ላይ ያዉላል፡፡
  • የምዘና መሣሪያዎችን ያዘጋጃል፤የተዘጋጁ የሙያ ምዘና መሳሪያዎች ሚስጥራዊነታቸው ተጠብቆ ለምዘና ተግባር መዋላቸውን ይከታተላል፡ ለአተገባበሩም አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡
  • ተመዝነው ለበቁ ተመዛኞች የምስክር ወረቀት ያዘጋጃል፣ለምዘናጣቢያዎችያሰራጫል፡፡
  • የምዘና ማዕከላትን ለመከታተልና ለመደገፍ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፡ አፈፃጸሙን ይከታተላል፡፡
  • በሙያ ብቃት ምዘና አተገባበር እና የሙያ ብቃት ምስክር ወረቀት አሰጣጥ ዙሪያ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን አጣርቶተገቢውን ውሳኔ ይሰጣል፡፡
  • የሙያ ብቃት መዛኞችን ከእንዱስትሪዎች በመስፈርቱ መሰረት በመመልመል የስነ ምዘና ሥልጠና በመስጠት የመዛኝነት የዕውቅና ሠርትፊኬት ይሠጣል፡፡
  • የምዘና ጣቢያዎችን በስታንዳርዱ መሠረት በመገምገም ብቁ ለሆኑት የምዘና ጣቢያነት ዕውቅና ፈቃድ ይሠጣል፡፡
  • የክትትልና ድጋፍ ሂደቱን በማጠናከር የምዘና  ጣቢያዎችን ማብቃት፣ የምዘናው አፈፃጸም ሪፖርት መሰብሰብ፤ ማጠናቀር፡ መረጃውን አደራጅቶ መያዝ፣ ግብረ መልስ መስጠት፡፡