በሙያ ብቃት ምዘና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የሚሰጡ ዋና ዋና ተግባራት
- የሙያ ብቃት ምዘና ጥያቄ ከምዘና ጣቢያዎች መቀበል፤
- ከየምዘና ጣቢያ የቀረበውን የተመዛኞች መረጃ በማጣራት፤በሙያ ዓይነትና ደረጃ መለየት፤
- የምዘና መርሃ ግብር ማዘጋጀት፤
- የምዘና በጀት ፕሮፖዛል ማዘጋጀት፤
- ሱፐርቫይዘሮችን መመደብ፣ማሳወቅና፣ ስምሪት መስጠትና መከታታል፤
- ምዘና ማካሄድና ጥራቱን ለማስጠበቅ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤
- የምዘናውን ውጤት ለተመዛኝ ግብረ መልስ መስጠት፤
- ከተመዛኞች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን መቀበልና መፍታት፤
- የብቃት ምዘና መረጃዎችን ከሱፐርቫይዘሮች መቀበልና ማደራጀት፤
- በየወቅቱ የተሰበሰቡ የብቃት ምዘና መረጃዎችን ወደ ዳታ ቤዝ ማስገባት፤
- የምዘና ውጤትና የሌሎች መረጃች ይጣራልኝ ጥያቄ ማጣራትና ምላሽ መስጠት፤
- የሙያ ብቃትን በምዘና በማረጋገጥ የብቃት ማረጋገጫ ሰርትፍኬት መስጠት፣
- የብቃት ማረጋገጫ ሰርትፍኬት ዕድሳት አገልግሎት መስጠት፣
- ሰርትፍኬት ይጣራልን ጥያቄዎችን ተቀብሎ ማጣራትና ምላሽ መስጠት፤
- ምትክ የብቃት ማረጋገጫ ሰርትፍኬት ጥያቄዎችን የቆይታ ጊዜያቸውንና ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን በማረጋገጥ መቀበልና ተተክ ሰርትፍኬት መስጠት፤
- የብቁ ተመዛኞችን መረጃ በሙያ ዓይነትና ደረጃ በመለየት ማደራጀትና ማጠናቀር
- የሰርትፍኬትና ምዘና አገልግሎት ክፍያ ማስከፈል
- የምዘና ጣቢያዎች ለምዘናዉ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥሩ የምክር አገልግሎት መስጠት፤
- ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት፤