የእቅ/በጀት/ዝግ/ ክት/ ግምገማ ዳይሬክቶሬት
- የሥራ ቡድኖችን ሥራ ያቅዳል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ውሳኔ በሚያሥፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣
- ባለሙያዎችን የአቅም ክፍተት በማጥናት አቅማቸው የሚገነባበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
- ለሥራ ቡድኖችና ባለሙያዎች የሚያስፈልጉ ግብአቶች እንዲሟሉ ያደርጋል፣
- የመሥሪያቤቱን ስትራቴጂክና አመታዊ እቅድና በጀት ዝግጅት፣ የክትትልና ድጋፍ፣ የግምገማና ግብረ መልስ ሥራዎችን በኃላፊነት ይመራል፣ ያስተባብራል፣
- የእቅድና በጀት ዝግጅትና ሪፖርት፣ የግምገማና ግብረመልስ ሥራዎች ውጤታማና ቀልጣፋ እንዲሆኑ ያሠራር ስርዓቶችን ይዘረጋል፣
- የጸደቀው እቅድና በጀት ለሥራ ክፍሎች በአግባቡ እንዲደለደል በማድረግ ያሳውቃል አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ግብረ-መልስ ይሠጣል፣
- የሥራ ክፍሎች የእቅድና በጀት ዝግጅት ሥራን እና አፈፃፀምን ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይገመግማል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፡፡
- የበጀት ዝውውር ጥያቄ ሲቀርብ አግባብነቱን በመመርመር የውሳኔ ሃሳብ ለበላይ ኃላፊው ያቀርባል ሲወሰንም ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
- በእቅድና በጀት አፈጻጸምና አጠቃቀም ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮች አማራጭ የመፍትሄ ሀሳብ በማመንጨት ለዉሳኔ ያቀርባል፣ ሲወሰን ተግባራዊ ያደርጋል፣